Tuesday, January 15, 2013

ነብዩ ሙሴና ኢትዮጵያ


ነብዩ ሙሴና ኢትዮጵያ

·         የሙሴ በኢትዮጵያ ላይ ሹመት ( የእስራኤላውያን ድርሳን ሙሴ ኢትዮጵያን 40 ዓመት ገዝቷል)
·         ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ እስከ ኢ የሩሳሌም መርቶ ያደረሳቸው ኢትዮጵያዊ ነው
·         የመጀመርይዋ የ እስራኤል ቀዳማዊ እመቤት ኢትዮጵያዊ ነበረች
·         የመጀመርያዎቹ ኦባማዎች ትውልደ ኢትዮጵያውን ናቸው
·        ሙሴን ሃይማኖት ያስተማረው ኢትዮጵይዊው ካህን ነው

1.     የሙሴ በኢትዮጵያ ላይ መሾም

በባለፈው ጽሁፌ ለመመልከት እንደሞከርነው ኢትዮጵያዊው ዝሪ አንድ ሚልዮን ሰራዊትና ሶስት መቶ ሰረገሎችን ይዞ ወደ እስራኤል መዝመቱንና በዚህም የተደናገጠው የእስራኤል ንጉስ ወደ ፈጣሪው ጽሎት ማድረሱን ጸሎትም ሲያደርስ ኢትዮጵያውያኑን " ታላቅ ሕዝብ " በማለት እንደጠራቸውና የ እንግሊዘኛው መጽሀፍ ቅዱስ ይሄንን ሰተርጉመው " The Great Ethiopians " The Great Nation " በማለት መሆኑን አይተናል

2መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 14:9 
"9 ኢትዮጵያዊውም ዝሪ አንድ ሚሊዮን ሰዎችና ሦስት መቶ ሰረገሎች ይዞ ወጣባቸው ወደ መሪሳም መጣ። 10 አሳም ሊጋጠመው ወጣ፥ በመሪሳም አጠገብ ባለው በጽፋታ ሸለቆ ውስጥ ተሰለፉ። 11 አሳም። አቤቱ፥ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አይሳንህም አቤቱ አምላካችን ሆይ፥ በአንተ ታምነናልና፥ በስምህም በዚህ ታላቅ ሕዝብ ላይ መጥተናልና እርዳን አቤቱ፥ አምላካችን አንተ ነህ ሰውም አያሸንፍህ ብሎ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።"

ታላቅ ሕዝብ የሚለውን ያዙልኝ

የአይሁድ የክርስትናና የታሪክ ሊቃውንት ደግሞ በሙሴና በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚደንቅ ታሪክ አላቸው:: አይሁዶች "ሙሴ ኢትዮጵያ ሄዶ ኢትዮጵያን አርባ አመት ገዝቷል" ብለው ሲከራክሩ የክርስትናና የታሪክ ሰዎች ደግሞ " ኢትዮጵያ ላይ እግዚአብሔር ሊሾመው ነበር እንጂ የኢትዮጵያ ንጉስ አልነበረም " ይላሉ
የክርስትና ሊቃውንት የሚጠቅሱት አንዱ መከራክርያ ይሄ ነው ሙሴ ሲና ተራራ ላይ በቆየ ወቅት እስራኤል የጥጃ ጣኦት አቁመው ለጥጃው መስገድ ጀመሩ:: እግዚአብሔርም በዚህ በጣም ተቆጣ:: ሕዝቡንም ሊያጠፋው እንደወደደና ሙሴንም ለሌላ ታላቅ ሕዝብ መሪ እንደሚያደርገው ገለጸለት ይሔ ከእስራኤል ውጭ ያለ  ሌላ ታላቅ ሕዝብ ማን ነበር?

ኦሪት ዘጸአት 32
7 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ከግብፅ ምድር ያወጣኸው ሕዝብህ ኃጢአት ሠርተዋልና ሂድ፥ ውረድ።
8 ካዘዝኋቸው መንገድ ፈጥነው ፈቀቅ አሉ ቀልጦ የተሠራ የጥጃ ምስል ለራሳቸው አደረጉ፥ ሰገዱለትም፥ ሠዉለትም። እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው አሉ ሲል ተናገረው
9 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ እኔ ይህን ሕዝብ አየሁት፥ እነሆም አንገተ ደንዳና ሕዝብ ነው።
10 አሁንም ቍጣዬ እንዲቃጠልባቸው እንዳጠፋቸውም ተወኝ አንተንም ለታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ አለው።

ይሔ ከእስራኤል ጋር የሚወዳደር ሌላ ታላቅ ሕዝብ ማን እደሆነ ጻድቅ የነበረው የእስራኤል ንጉስ ቀድሞ ተናግሮታል(2መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 14:9):: በዘመነ ብሉይ የነበረው ነብዩ አሞጽም የተናገው ይጠቀሳል ትንቢተ አሞጽ 97 "የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያውያን ልጆቼ አይደላችሁምን?'ስለዚህ ሙሴ ሊሾምበት የነበረው ታላቅ ሕዝብ ኢትዮጵያ እንደነበረች ጥርጥር የለውም::
የሚደንቀው ግን የእስራኤላውያኑ እይታ ነው የእስራኤላውያን የቀደሙ የታሪክ ሊቆቻቸውን ዜና መዋእል በመጥቀስ " ሙሴ ኢትዮጵያን አርባ አመት ገዝቷታል" ይሉናል ይህንንም የጂውሽ ኢንሳይክሎፒዲያ (The Jewish Encyclopedia: A Descriptive Record of the History ..., Volume 9, page 48 edited by Isidore Singer, Cyrus Adle)እንዲህ ሲል ያትተዋል

King in Ethiopia.
The fugitive Moses went to the camp of King Nikanos, or Kikanos, of Ethiopia, who was at that time besieging his own capital, which had been traitorously seized by Balaam and his sons and made impregnable by them through magic. Moses joined the army of Nikanos, and the king and all his generals took a fancy to him, because he was courageous as a lion and his face gleamed like the sun ("S. Y." P. 116a; comp. B. B. 75a). When Moses had spent nine years with the army King Nikanos died, and the Hebrew was made general. He took the city, driving out Balaam and his sons Jannes and Jambres, and was proclaimed king by the Ethiopians. He was obliged, in deference to the wishes of the people, to marry Nikanos' widow, Adoniya (comp. Num. xii.), with whom he did not, however, cohabit ("D. Y." l.c.; "S. Y." p. 116b). Miriam and Aaron spoke against Moses on account of the Cushite (Ethiopian) woman whom he had married. He was twenty-seven years of age when he became king; and he ruled over Ethiopia for forty years, during which he considerably increased the power of the country. After forty years his wife, Queen Adoniya, accused him before the princes and generals of not having cohabited with her during the many years of their marriage, and of never having worshiped the Ethiopian gods. She called upon the princes not to suffer a stranger among them as king, but to make her son by Nikanos, Munahas or Munakaros, king. The princes complied with her wishes, but dismissed Moses in peace, giving him great treasures. Moses, who was at this time sixty-seven years old, went from Ethiopia to Midian (ib.).
http://www.jewishencyclopedia.com/articles/11049-moses
2.    የመጀመርያዋ የእስራኤል ቀዳማዊ እመቤት የሙሴ ሚስት ኢትዮጵይዊቷ ሲፓራ ነበረች
ኢትዮጵያን አትንኩ !!!
ከመጽሀፍ ቅዱስ እንደምንረዳው ሙሴ በምድር ሁሉ ካሉት ሰዎች " እጅግ ትሁት " እንደነበረና ( ዘኁ 12:3) በምድር ካሉ ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔር አፍ ለአፍ እንደሚናገረውና የእግዚአብሔርንም መልክ ያየ ብቸኛው ጻድቅ እንደነበረ በሚገባ ተገልጿል( ዘኁ 12:8) ታድያ ይህ ቀረህ የማይባለው ጻድቅና የሕግ መምህር ሙሴ መርጦ ያገባት ኢትዮጵያዊቱ ሲፓራን ነው በዚህም እስራኤላዊያኑ በማያገባቸው ነገር ገብተው ተናደዱ ይሄኔ " እንዴት ይቺን ኔግሮ ያገባል ስንት እስራኤል ቆንጆ ሞልተን" ብለው ይሆናልሊቀ ካህናቱ አሮንና ማርያም በይፋ ቁጣቸውን ገለጹ ግን ምን ያደርጋል:: ሙሴ እንዴት ኢትዮጵያዊቷን ያገባል ብላ ያንጎራጎረችው ማርያም ስለዚህ ድፍረቷ በለምጽ ተቀጣች ኢትዮጵያን አትንኩ !!!
ኦሪት ዘኍልቍ 12: 1-
1 ሙሴም ኢትዮጵያይቱን አግብቶአልና ባገባት በኢትዮጵያይቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ ላይ ተናገሩ።
9 እግዚአብሔርም ተቈጥቶባቸው ሄደ።
10.ደመናውም ከድንኳኑ ተነሣ እነሆም፥ ማርያም ለምጻም ሆነች፥ እንደ አመዳይም ነጭ ሆነች አሮንም ማርያምን ተመለከተ፥ እነሆም፥ ለምጻም ሆና ነበር።
11 አሮንም ሙሴን፦ ጌታዬ ሆይ፥ ስንፍና አድርገናልና፥ በድለንማልና እባክህ፥ ኃጢአት አታድርግብን።

3.     የኢትዮጵያዊቷ ሲፓራ ልጆች -- የመጀመርያዎቹ ኦባማዎች
ሙሴ ከኢትዮጵያዊት ሚስቱ ሁለት ልጆችን ወለደ:: እነዚህም ልጆች ስማቸው ጌርሳምና አልዓዛር ነበሩ:: ዘጸ 18:2 “በዚያን ጊዜ የሙሴ አማት ዮቶር መልሶአት የነበረውን የሙሴን ሚስት ሲፓራን ሁለቱንም ልጆቿን ወሰደ።”
እነዚህ ልጆች ሲያድጉ ባለስልጣን ሆነው ተሾሙ:: ቁጥራቸውም ታቦተ ጽዮንን ከሚያገለግሉት ከነገደ ሌዊ ሆነ::


መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 23
14.የእግዚአብሔርም ሰው የሙሴ ልጆች በሌዊ ነገድ ተቈጠሩ።
15 የሙሴ ልጆች ጌርሳምና አልዓዛር ነበሩ።
16 የሙሴ ልጅ የጌርሳም ልጅ ሱባኤል በቤተ መዛግብት ላይ ተሾሞ ነበር።

ከነገደ ሴምና ከኢትዮጵያውያን ተወልደው በ እስራኤል ላይ ባለስልጣን የሆኑ የመጀመርያ ነጭና ጥቁሮች ( ኦባማዎች)


4.     እስራኤልን ከግብጽ ወደ ኢየሩሳሌም እየመራ የወሰዳቸው ኢትዮጵያዊው ኦባብ

ሙሴ እስራኤልን ባሕር ከፍሎ ያሻገረ ታላቅ ነብይ ነበር መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ግን ሌላ የሚገርም ታሪክ ተጽፏል ባሕረ ኤርትራን ከፍሎ ያሻገረው ታቁ ነብይ ወደ ኢየሩሳሌም ሕዝቡን ይዞ የሚሄድበት መንገድ ጠፋው ምንም እንኳን ቀን በአምደ ደመና ሌት ደግሞ በአምደ ብርሃን እየተመራ ሕዝቡን ይዞ ቢጓዝም ለሙሴ ሌላ ሰው መንገዱን ያሳያው ዘንድ ግድ ነበር ይሄውም ሰው ኢትዮጵያዊው ኦባብ ራጉኤል ይባላል:: ሙሴ በራሱ አንደበት እንተ ለኛ ለእስራኤላውያን " አይኖቻችን ነህ " ብሎ የመሰከረለትና ሕዝበ እስራኤልን ይዞ ኢየሩሳሌም ያገባቸው ታቦተ ጽዮንንም ማደርያዋን ያዘጋጅ የነበረ ሃያል ኢትዮጵያዊ :: የኢትዮጵያዊቷ የሙሴ ሚስት ወንድም ኦባብ ወልደ ራጉኤል

ዘኁ 10:29
29ሙሴም የሚስቱን አባት የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ ኦባብን፦ እግዚአብሔር፦ ለእናንተ እሰጠዋለሁ ወዳለው ስፍራ እንሄዳለን እግዚአብሔር ስለ እስራኤል መልካምን ነገር ተናግሮአልና አንተ ከእኛ ጋር ና፥ መልካምን እናደርግልሃለን አለው።
30 እርሱም፦ አልሄድም፥ ነገር ግን ወደ አገሬና ወደ ዘመዶቼ እሄዳለሁ አለው።
31 እርሱም፦ እባክህ፥ በምድረ በዳ የምንሰፍርበትን አንተ ታውቃለህና፥ እንደ ዓይኖቻችንም ትሆንልናለህና አትተወን
32 ከእኛም ጋር ብትሄድ እግዚአብሔር ከሚያደርግልን መልካም ነገር ሁሉ እኛ ለአንተ እናደርጋለን አለ።
33 ከእግዚአብሔርም ተራራ የሦስት ቀን መንገድ ያህል ተጓዙ የእግዚአብሔርም የኪዳኑ ታቦት የሚያድርበትን ስፍራ ይፈልግላቸው ዘንድ የሦስት ቀን መንገድ ቀደማቸው።

ታላቂቷ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!!

ይቀጥላል

No comments:

Post a Comment